ቅምሻ
ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
“ክቡር ድንጋይ” አንባቢውን ከመጀመሪያው ገጽ ጀምሮ ወደ ምስጢራዊና አስደናቂ ዓለም የሚወስድ ልቦለድ ነው። ደራሲው ይስማዕከ ወርቁ በተለየ የ አቀራረብ ቅርጽ የያዘ ልቦለድ ነው። ሰውነትን፣ እውነትን መገፋትን ያሳያል።
ታሪኩ የሚጀምረው በአስገራሚ ሁኔታ ውስጥ ነው። በመጽሐፉ ውስጥ ዶክተር ዲዲሞስ በአስማት ከሰውነት ወደ ውሻነት መለወጡን ይነግረናል። ነገር ግን በአስማት እንደገና ወደሰውነት መለወጥ አስማቱን አያውቀውም። ገፀ-ባህርይው ግን አእምሮው እንደቀድሞው የሰው አእምሮ መሆኑን ያውቃል። በዚህ ልቦለድ ውስጥ ዘመኑን ይተነትናል።
ከዚያም የራሱን አዲስ ሁኔታ ለመረዳት ይሞክራል። ሰው እያለ የማያስተውላቸውን የውሻ ስሜቶችና ችሎታዎች አሁን በራሱ ላይ ይለማመዳቸዋል። በጨለማ ውስጥ ማየት፣ ድምፆችን በጥልቀት መስማትና ሽታን መለየት የአዲስ ሕይወቱ ክፍሎች ይሆናሉ።
ከውሻነት ወደሰውነት እንደገና ለመለወጥ የሚያሳይ ከፍተኛ ትግል የሚጠይቅ መጽሐፍ ነው።
ደራሲው ግን በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ያስጠነቅቃል። ምን ብሎ? “በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የሚገኙትን የአስማት ቃላት በመሞከር ለሚመጣው ችግር ደራሲው ተጠያቂ አይደለም” በማለት።
“ክቡር ድንጋይ” በይስማዕከ ወርቁ የተደረሰ ልቦለድ ሲሆን፣ ደራሲው አዲስና የተለየ የትረካ መንገድ በመጠቀም ታሪኩን ያቀርባል። ስለ ደራሲው የፈጠራ ችሎታ፣ ስለ የአጻጻፍ ስልቱ እና በቀደሙት ሥራዎቹ ያሳየው ልዩ አቀራረብ በጥበብ የቀረበ ሥራ ነው። ታሪኩ ከተለመደው የልቦለድ ትረካ የተለየ ሲሆን፣ እውነታንና ምናብን በማዋሃድ ማህበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። በተለይም ዋናው ገጸ ባህርይ በአስገራሚ ሁኔታ ሰውነትን ከውሻነት አደባልቆ በመያዙ፣ የታሪኩን ምስጢራዊ እና ምናባዊ ገጽታ ያጠናክራል።
ደራሲው በተለያዩ ሥራዎቹ የከተማዎችንና የኢትዮጵያን ታሪክ ከልቦለድ ትልሙ ጋር በማስተሳሰር የሚያቀርብበትን መንገድም ያብራራል። ክቡር ድንጋይ መጽሐፍ በእንግሊዝ ሀገር “The Lost Spell” በሚል ተተርጉሞ የተሸለመ መጽሐፍ ነው።
የቀጣዩን ገጽ ለማወቅ መጽሐፉን ያንብቡ።

ውይይቱን ይቀላቀሉ