ቅምሻ
የኦጋዴን ድመቶች በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
አንዳንድ መጻሕፍት ታሪክ ይነግራሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንባቢውን ወደ ታሪኩ ውስጥ ጎትተው ይከቱታል። “የኦጋዴን ድመቶች” እንደዚህ ያለ መጽሐፍ ነው።
በይስማዕከ ወርቁ የተደረሰው ይህ ልብ ወለድ የክቡር ድንጋይ ተከታይ ነው። ዶክተር ዲዲሞስ፣ አያንን ያገኛታል። የሰውን ሕይወት- ከታሪክ፣ በትዝታና ከምናብ ጋር በሚያገናኝ የተለየ የተረክ ዓለም ውስጥ ያስገባል። የተለመደውን እውነታ በአንድ በኩል፣ ምናብን በሌላ በኩል አቁሞ ከሁለቱ መካከል ያለውን ድንበር እንድንጠይቅ ያደርገናል።
ይህ ታሪክ ለመዝናናት ብቻ የሚነበብ አይደለም። ስለ ምናስታውሰውና ስለምንረሳው፣ ስለ ሰው እና ስለ ዓለም ያለን ግንዛቤ የሚያሰለስል መጽሐፍ ነው። የርዕሱ ምስጢርም እንዲሁ አንባቢውን ከመጀመሪያው ይይዛል፣ “የኦጋዴን ድመቶች”።
ይህ ታሪክ ልብን ሰቅዞ ብቻ አይዝም፣ ከገጾቹ መካከል የተደበቀውን ዓለም ያስፈልጋል እንጂ። “የኦጋዴን ድመቶች” ለሚያነብ ብቻ ሳይሆን፣ ካነበበ በኋላ ለሚያስብ አንባቢ የተጻፈ ልብወለድ ነው። አንብበው ካበቁ በኋላ፤ ምናልባት ከመጽሐፉ በኋላ እርስዎም ዓለምን በተመሳሳይ ዓይን አትመለከቱትም።

ውይይቱን ይቀላቀሉ