ቅምሻ
ዴርቶጋዳ በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
በዚህ በተራቀቀና በህዋ ቅርምት (space exploration) ዘመን በአማርኛ ተፅፎ ለመነበብ በቂ ብቃት ያለው ፈር ቀዳጅ ልቦለድ።
ቋንቋው እስከነ ታሪክ አወቃቀሩ እንከን አይወጣለትም፤ ከዚያም ጋር ከማንም ሌላ ፀሐፊ የሚለየው ይስማዕከ የራሱ የጽሑፍ ዘይቤ (style) አለው።
ትረካውን ከምዕራፍ ወደ ምዕራፍ ስንከተለው ልብ አንጠልጥል ነው፤ የብዙ ውስብስብ ታሪኮች ጭማቂ ሆኖ አንድ ገፅ ስንገለብጥ አዲስ ነገር እናገኛለን፤ በድርጊት የተሞላ ነው (ፍጥነቱ)።
ሳይንስ፣ ስለላ፣ ሮማንቲክና ታሪካዊ ልቦለድም ጭምር ነው። ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን ያስተሳሰረ ተሻጋሪ ልቦለድ ነው።
ከሚያውጠነጥናቸው ሀሳቦች አንዱ ለቁሳዊ ሀብትና ለአዕምሮአዊ ሀብት ስለሚደረግ ትንቅንቅ፣ እንዲሁም ሀገር ወዳድነት ነው፤ ማን ለራሱ ሲል ምን ተከፍሎት ማንን ወይስ ምንን ይሸጣል? የተቀረውን አንባቢ ከጽሑፉ ጋር ቢወያይበት ይመረጣል።

ውይይቱን ይቀላቀሉ