ወደ ዋናው ይዘት ይሂዱ / Skip to main content

ተልሚድ (Telmid)

ግዢው ወደ Amazon ይወስድዎታል፤ ወደዚህ ገጽ ለመመለስ የአሳሽዎን "ተመለስ" የሚለውን ቁልፍ ይጠቀሙ።

ቅምሻ

ተልሚድ የተባለው መጽሐፍ፣ ነፍስን ከራስ ጋር የሚሰፋ ልብወለድ ነው።

ታሪኩ የሚዳስሰው የሰው ልጅ ከራሱ ጋር የሚያደርገው ረጅም በጣር የተሞላ ጉዞ ነው። አንዳንድ ጉዞዎች የሚጀምሩት ከምንም ነገር ነው፤ የሚያበቁት ግን በነፍስ ውስጥ ነው።

ተልሚድ የአንድ ሰው ታሪክ ብቻ አይደለም። የሚሸሽ ሰው፣ ሰውነትን የሚፈልግ ሰው፣ የሚያልም ሰው እና በመጨረሻም ራሱን ለመረዳት የሚሞክር ሰው ታሪክ ነው። ተልሚድ ከኢትዮጵያ ተነስቶ በስደት ውስጥ አልፎ፣ ግሪክ ደርሶ ከአኒያና ጋር ይገናኛል፤ በዚያም የሕይወቱ አዲስ ምዕራፍ ይከፈታል። አኒያና በውስጡ የያዘውን ጥበብ ምንጩ ነበረች።

ነገር ግን የተልሚድ ታሪክ የመንገድ ታሪክ ብቻ አይደለም። በውስጡ የተደበቀው ጥያቄ «ሰው በእውነት ምን ይፈልጋል?» የሚለው ነው። ምኞቶች እንደ ሰንሰለት ሰውን ወደ የተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጎትቱት፣ ተልሚድ ግን ከራሱ ምኞት ጋር የተለየ ትግል ውስጥ ይገባል።

ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል። ለመጻፍ የነበረው ትልቅ ሕልም ግን በቀላሉ አይሳካም። ሌሎች ታሪኮችን ይጽፋል፤ የራሱን ሕይወት መሠረት ያደረገው ታሪክ ግን እንዳልተጠናቀቀ ጥያቄ ከኋላው ይከተለዋል። በመጽሐፉ ውስጥ ስደት የቦታ መለወጥ ብቻ አይደለም፤ ትውስታም አንድ ዓይነት ጉዞ ሆኖ ይከተለዋል። ሰው ከትናንቱ ሊሸሽ ቢችልም፣ ትውስታውን ግን ይዞ ይጓዛል። ይህም ተልሚድን ከውጭው ዓለም ብቻ ሳይሆን ከውስጡም ጋር የሚያጋጭ ገጸ-ባህርይ ያደርገዋል።

ተልሚድ ሲነበብ አንድ ታሪክ ብቻ አይከተልም፤ ጥያቄዎችን ይከተላል። ሰው የሚሸሸው ከቦታ ነው ወይስ ከራሱ? ምኞት ነፃነት ነው ወይስ ሰንሰለት? የሚያስታውሰን ትውስታ ነው ወይስ የሚረሳን ጊዜ? ሰው የራሱን ታሪክ መጻፍ ይችላልን? እነዚህን ጥያቄዎች መልሱን ለማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ የራስዎን መልስ ለመፈለግ ወደ ተልሚድ ጉዞ ይግቡ።

«ተልሚድ» የሁላችንም ታሪክ ነው።

ውይይቱን ይቀላቀሉ

አስተያየት ይስጡ

ኢሜይልዎ አይታተምም። አስፈላጊ መስኮችን ይመልከቱ *